ኮቪድ - 19 ላይ ተጨማሪ ገጾች

ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ - 19) ምንድነው?

የበሽታው ስያሜ COronaVIrus Disease 2019 ወይንም ኮቪድ-19 ሲሆን, የበሽታው አምጪ ቫይረስ Severe Acute Respiratory Syndrome Coronavirus 2 (SARS – CoV2) ተብሎ ይታወቃል::

‘ኮሮና’ የላቲን ቃል ሲሆን ዘውድ ማለት ነው:: ኮሮና ቫይረስ በሽታው የሚገኝበትን የቫይረስ ቤተሰብ የሚያመለክት ሲሆን ዘውድ መሰል ቅርጽ ስላለው የተሰጠ ስያሜ ነው::

የተለያዩ የኮሮና ቫይረስ አይነቶች ሲኖሩ እነዚህም ጉንፋን MERS (Middle East Respiratory Syndrome) እና SARS (Severe Acute Respiratory Syndrome) የመሳሰሉት ናቸዉ ::

ኮቪድ-19 በቅርቡ የተከሰተ ሲሆን የሰው ልጆች የመተንፈሻ አካል የሚያጠቃ በሽታ ነው::

ቫይረሱ በሰውነታችን ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?

1

ቫይረሱ ወደሰውነታችን በአፋችን፥ በአይናችን ወይም በአፍንጫችን ይገባል

2

ቫይረሱ ወደ ሰዉነታችን ከገባ በኃላ፤ ወደ ኋለኛዉ አፍንጫችን ክፍልና ወደ ጎሮሮ ስስ ሽፋንጋ /mucous membranes/ይሰራጫል፡፡ይዛመታል፡፡

3

ዘውድ በሚመስሉ ነጠብጣቦች አማካኝነት የሰውነታችን ሴሎች ውስጥ ይገባል:: በዚህም የሰውነታችንን በሽታ የመዋጋት አቅም በመጉዳት ራሱን እያባዛ ሰውነታችንን መቆጣጠሩን ይቀጥላል::

4

4

ከዚያም ቫይረሱ ከጉሮሮ ጀርባ ወደታች ወደ ብሮንኪያል ቲዩብስና/bronchial tubes/ ወደ ሳንባ ይወርዳል፡፡  የመተንፈሻ ሽፈንንም ይጎዳል፤ እብጠትም ያስከትላል፡፡

ኢንፌክሽኑ በጣም የከፋ ከሆነ የአየር መተላለፊያ ሽፋን አልፎ ወደአየር መተላለፊያው መጨረሻ ወደሆነው የጋዝ ልውውጥ ክፍሎች ይሄዳል፡፡

5

ሳንባችን ኢንፍላሜሽን የሚፈጥሩ ነገሮችን ወደታችኛው ክፍል ወደሚገኙት የአየር ከረጢቶች በማፍሰስ የሳንባ ምች በመፍጠር ለዚህ ወረራ ምላሽ ይሰጣሉ ፡፡

6

በኢንፍላሜንሽን የተሞላው ሳንባ በደም ፍሰት ውስጥ በቂ ኦክስጅንን ማግኘት አይችልም፡፡ ይህም ኦክስጅንን የመውሰድ አና ካርቦን ዳይኦክሳይድን የማስወገድ ችሎታን ይቀንሳል፡፡ ብዙ የአካል ክፍሎችም በኦክስጂን እጥረት፣ በኢንፍላሜሽን እና septic shock ምክንያት መሥራት ያቆማሉ፡፡

ከቀላል እስከ መካከለኛ ህመም ምልክቶች

ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ የሚጀምሩት በጉሮሮ ፣ ጀርባ ላይ በቆሰለ ጉሮሮ እና በደረቅ ሳል ነው፡፡ የሰውነታችን የመከላከያ ሂደት/immune system/የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት ትኩሳትን ያስከትላል፡፡

ከፍተኛ ደረጃ ህመም ምልክቶች

የማያቋርጥ ሳል

ይህም ማለት ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ ማሳል፣ ወይም በ24 ሰዓታት ውስጥ 3 ወይም ከዚያ በላይ ጊዜያት ማሳል ነው፡፡ አንድ ግለሰብ አብዛኛውን ጊዜ ሳል ካለው ከወትሮው የከፋ ሊሆን ይችላል፡፡

ከፍተኛ የሆነ ሙቀት

ሰውነታችን ቫየረሱን ለመዋጋት በሚያደርገው ጥረት የሰውነታችን ሙቀት በዛው ልክ ይጨምራል፡፡

የትንፋሽ እጥረት

በሳንባ ውስጥ ያለው ንፍጥ መሰል ሽፋን በአየር መተላለፊያዎች በኩል አየር እንዳይንቀሳቀስ ያደርጋል፤ ይህም መተንፈስን ከባድ ያደርገዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የትንፋሽ እጥረት፣ የመተንፈስ ችግርና የድካም ስሜት ያስከትላል፡፡

ኮቪድ-19 ምን ያክል ገዳይ ነው?

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ በኮቪድ-19 ከተጠቁት ሰዎች ዉስጥ የህመም ምልክቱ 80 በመቶ ላይ ቀላል በ13 በመቶ ከባድ እና በ6 በመቶ አስከፊ መሆኑን ያሳያል፡፡
ኮቪድ-19 በጣም አስከፊ ካልሆነና ጥቂት የህብረተሰቡን ክፍል ብቻ የሚገድል ከሆነ ታድያ ለምንድዉ በጣም አደገኛ የሚሆነው?
ኮቪድ-19 ከዚህ በፊት ከሚታወቁት እንደ ሳርስ-ኮ፟ቭ እና ሜርስ-ኮ፟ቭ ወረርሽኞች በይበልጥ ፍጥነት እና በቀላሉ የሚዛመት መሆኑ ነው፡፡

ከታመሙ ሊወስዷቸው የሚገቡ እርምጃዎች

እነዚህ ተራ ቁጥር ከ1-5 የተመለከቱት በኢትዮጵያ በሽታዉን ለመከላከል የሚተገበሩ ናቸው፡፡ ከዚህ የተለየ ሁኔታ ሲያጋጥም በአቅራብያችሁ ወዳለው የጤና ባለስልጣን  በመሄድ የበሽታውን ምልክቶች ምርመራ እና መረጃ ማሳወቂያ መመሪያወችን ይጠይቁ፡፡

1. እራስዎትን ለዋና ዋና የኮቪድ-19 ምልክቶች ማለትም ትኩሳት ደረቅ ሳል እና የትንፋሽ ማጠር ካለብዎ ይመርምሩ፡፡

2.ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች አንዱ ወይም ሁሉም ከተሰማዎት 8335 ደውለው ምልክቶቹን ያሳውቁ፡፡

3.የ8335 ጥሪ ረጅም መጠበቂያ ጊዜ ሊኖረው ሰለሚችል በትዕግስት መስመር ላይ ይጠብቁ፡፡

4.የጥሪ ተቀባዩ ተጨማሪ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ካሉ ይወስናል፡፡

5.የጥሪ ተቀባዩ በሽታው አለብዎት ብሎ ካመነ የህመምዎን ሁኔታ ሊያረጋግጥ የሚችል የምርመራ እና ክትትል ቡድን ወደ አከባቢዎ የሚልክ ይሆናል፡፡